ቢዝነስ

ረጅም ጊዜ የሚፈጅ አሰራር በሲሚንቶ የንግድ ሰንሰለትና የዋጋ መናር ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ እያሳረፈ ነው – ኢ/ር ታከለ ኡማ

By Mekoya Hailemariam

January 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ረጅም ጊዜ የሚፈጅ አሰራር በሲሚንቶ የንግድ ሰንሰለትና የዋጋ መናር ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ እያሳረፈ እንደሚገኝ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከ ኡማ አስታወቁ፡፡

የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ቀድመው ገንዘብ የተቀበሉባቸው ከ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ቶን በላይ ውዝፍ የሲሚንቶ እዳ እንዳለባቸው ጠቅሰዋል፡፡

ለተጠቃሚዎች ለማድረስ ረጅም ጊዜ የሚፈጅ አሰራር በሲሚንቶ የንግድ ሰንሰለትና የዋጋ መናር ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ እያሳረፈ ከመገኘቱም በላይ በጥሬ ግብአት አቅርቦት ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ አሳርፏል ነው ያሉት ሚኒስትሩ።

ለእነዚህ ከፍተኛ የሲሚንቶ ውዝፍ እዳ ላለባቸው ፋብሪካዎችም ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው በፍጥነት ወረፋ ለያዙ ደንበኞች አቅርበው እንዲያጠናቅቁና እዳቸውን ምርት በመጨመር እንዲጨርሱ ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው ነው ያስረዱት።

በቅርቡም የእጅ በእጅ የሲሚንቶ ሽያጭን ማቀላጠፍ የሚችል መመሪያ ከንግድ ሚንስቴር፣ ከሚመለከታቸው ተቋማትና አምራች ፋብሪካዎች ጋር በጋራ በመሆን ፀድቆ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።