ስፓርት

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ

By Meseret Demissu

January 02, 2022

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል፡፡

ከዚህ ቀደም በተፈጠረው የአሰራር ክፍተት ምክንያት ከኢትዮጵያ አግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚነት ታግደው የቆዩት ወይዘሮ ሶፍያ አልማሙን ወደ ስራ አስፈፃሚነት ቦታቸው እንዲመለሱ የውሳኔ ሀሳብ ለጉባኤተኛው ቀርቦ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

በተጓደለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንትነት ቦታ ላይ በአሁኑ ሰዓት የዋልያዎቹ ቡድን መሪ በመሆን በካሜሩን የሚገኙት አቶ አበበ ገላጋይ ለውሳኔ ቀርበው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።

በተጨማሪም አቶ ዮሴፍ ካሣ የዲሲፕሊን ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል።

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በመጪው መጋቢት ወር 2014 በአዲስ አበባ እንደሚደረግ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!