አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመንግስትን ጥሪ ተከትለው ከመላው ዓለም ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ ላሉ እንግዶች ልዩ የዳያስፖራ የቅድመ ክፍያ ካርዶችን ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
ባንኩ በተለያየ የብር መጠን የቅድመ ክፍያ ካርዶችን ያዘጋጀ ሲሆን፥ ተገልጋዮች ካርዶቹን በአቻ የውጭ ምንዛሬ መጠን በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ወይም ከዓለም አቀፍ ካርዳቸው በማዛወር መግዛት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
ልዩ የዳያስፖራ ካርዶችን የሚጠቀሙ ተገልጋዮች ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 23 ቀን 2014 ዓ.ም በፖስ አማካኝነት ግብይት በሚፈጽሙበት ጊዜ ከ2 ነጥብ 5 እስከ 7 በመቶ የሚደርስ ከግብይት ተመላሽ ያገኛሉም ነው የተባለው።
ባንኩ ለዳያስፖራው ያዛጋጃቸው የክፍያ ካርዶች፣
• ፕላቲኒየም (ከ1 ሺህ ዶላር በላይ የሚገዛና 7 በመቶ ተመላሽ የሚያስገኝ)፣
• ጎልድ (ከ200 እስከ 1 ሺህ ዶላር የሚገዛና 5 በመቶ ተመላሽ የሚያስገኝ) እና
• ዋሌት (በ100 ዶላር ተገዝቶ 2 ነጥብ 5 በመቶ ተመላሽ የሚያሥገኝ) ካርዶች መሆናቸውን የባንኩ መረጃ ያመላክታል።
ካርዶቹ በዋናነት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተርሚናሎች በአዲስ አበባ፣ ደሴ፣ ድሬዳዋ፣ ጎንደር፣ ሃዋሳ፣ ባሕርዳር እና አርባ ምንጫ አውሮፕላን ማረፊያዎች፥ አዲስ አበባ ውስጥ ደግሞ በወዳጅነት፣ እንጦጦ እና አንድነት ፓርኮች እንዲሁም በተመረጡ የባንኩ ቅርንጫፎች ላይ በተተከሉ የካርድ መሸጫ ድንኳኖች ይገኛሉ ተብሏል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!