አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ አምስት ወራት ከቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ኤክስፖርት 525 ነጥብ 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
በበጀት ዓመቱ አምስት ወራት 114 ሺህ 335 ነጥብ 63 ቶን የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት በመላክ 367 ነጥብ 56 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ÷ 138 ሺህ 552 ነጥብ 16 ቶን ወይም 121 በመቶ በመላክ 525 ነጥብ 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወይም 143 በመቶ ገቢ ተገኝቷል፡፡
አፈጻጸሙ ባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተላከው ጋር ሲነጻጸር በመጠን 51 ሺህ 298 ነጥብ 87 ቶን ወይም 58 ነጥብ 79 በመቶ በገቢ ደግሞ 244 ነጥብ 50 ሚሊየን ዶላር ወይም 86 ነጥብ 98 በመቶ ጭማሪ ተመዝግቧል መባሉን ከቡናና ሻይ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የቡና አፈጻጸም በአምስት ወራት ውስጥ 108 ሺህ 35 ነጥብ 70 ቶን ቡና በመላክ 358 ነጥብ 81 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 133 ሺህ 113 ነጥብ 74 ቶን በመላክ 515 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜርካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡
ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን 51 ሺህ 546 ነጥብ 65 ቶን እና በገቢ ደግሞ የ 240 ነጥብ 81 ሚሊየን ዶላር ጭማሪ ታይቶበታል ተብሏል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!