Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ በተገኙበት የህዳሴ ግድብ ግንባታን የተመለከተ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተገኙበትና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን የተመለከተ ውይይት ተካሄደ ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት ግድቡን በተመለከተ እየተደረጉ ያሉ ድርድሮች አካሄድ እና አቅጣጫ ላይ ምክክር ይደረጋል ተብሏል።

በውይይቱ ሚኒስትሮች፣ የተደራዳሪ ኮሚቴ አባላት፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፈረንጆቹ የካቲት 12 እስከ የካቲት 13 ቀን 2020 በዋሽንግተን ዲሲ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅን በተመለከተ ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ለማዘጋጀት ሲካሄድ የነበረው ውይይት ሳይቋጭ መቅረቱ የሚታወስ ነው።

በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብፅ እና ሱዳን ልዑካን ጋር የተደረገውን የህግ ማዕቀፍ ድርድር ውጤት በዋሽንግተን ዲሲ ከገመገመ በኋላ ሌላ ዙር ውይይት ቀጥሎ ሲካሄድ ነበር።

ሆኖም ሀገራቱ የግድቡን የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ በተመለከተ ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ለማዘጋጀት ሲያደርጉት የነበረው ውይይት ሳይቋጭ መቅረቱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version