አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ነዋሪዎች በሀገሪቱ እየተከናወነ ያለውን ለውጥ በመደገፍ ዛሬ የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ።
በዞኑ 15 ወረዳዎችና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ነዋሪዎቹ ሰልፍ በማካሄድ፣ የፅዳት ዘመቻ እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን በማከናወን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቲር ዶ/ር ዐብይ አህመድ እና የለውጥ አመራሩ በሃገሪቱ እያደረጉት ያለውን የለውጥ ስራ በመደገፍ ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል።