አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዝነው በጀት ዓመት የመጀመሪያው 5 ወራት ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ምርት የወጪ ንግድ 203 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በ5 ወራት ውስጥ ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ምርት 215 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነው 203 ሚልየን ዶላር ወይም የእቅዱን 94 በመቶ ማግኘት የተቻለው፡፡
ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወራት ክንውን ጋር ሲነፃፀር የ45 ነጥብ 85 ሚሊየን ዶላር ወይም የ29 ነጥብ 21 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል፡፡
ለችግር ሳንበገር ኢትዮጵያን ከድህነት ለማውጣት መስራት የህልውና ትግላችን አካል ነውም ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!