Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቻይና የአፈር ለምነት ማሻሻል የሚያስችል የተፈጥሮ ማዳበሪያ በኢንዱስትሪ ደረጃ እያመረተች ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የዕጽዋት ተረፈ ምርት እና የደን ብስባሽ በኢንዱስትሪ ደረጃ በማምረት የሀገሪቷን የአፈር ለምነት ለመመለስ እየሰራች መሆኑ ተገለጸ፡፡

ቻይና ከዕጽዋት ተረፈ ምርት የምታመርተው “ሂዩሚክ አሲድ” በመባል የሚታወቀው ማዳበሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተረጋገጠ እና ለከባቢ አየር ተስማሚ መሆኑ መረጋገጡም ተመላክቷል፡፡

በቻይና ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል ምኅንድስና ኮሌጅ ፕሮፌሰር የሆኑት ቲያን ዩዋንዩ ÷ ሀገሪቷ ከፈረንጆቹ 2012 ጀምራ “ሂዩሚክ አሲድ” ን በኢንዱስትሪ ደረጃ በማምረት የሰብል ምርታማነቷን ከማሳደጓም በላይ ዘላቂ የአፈር ለምነትን እና የሥነ ምህዳር ሕይወትን ለማስቀጠል እንደቻለች ነው የገለጸው፡፡

ባለፉት 3 ዓመታት ቻይና ወደ 667 ሺህ ሄክታር መሬት በኢንዱስትሪ ደረጃ የተመረተ የተፈጥሮ ማዳበሪያ በመጠቀም አፈሯን ማከም መቻሏን ሲጂቲ ኤን አመላክቷል፡፡

ቀደም ባሉት ጊዜያት የቻይና ገበሬዎች የሰብል ተረፈ-ምርቶቻቸውን እና የደን ብስባሾችን ለአፈር ለምነት በማዳበሪያነት ከመጠቀም ይልቅ ሰብስበው የማቃጠል ልምድ ነበራቸው፡፡

ይህም የአየር ንብረት ሲበክል ከመቆየቱም በላይ የሐብት ብክነት ሆኖ መቆየቱም በመረጃው ተመላክቷል፡፡

ቲያን ÷ ከጥናት ቡድኑ ጋር በመተባበር ከፍተኛ የብረት ማዕድን ያለው አፈር ማከም የሚያስችል የጥናት ውጤት ማበርከታቸውንም ጠቁሟል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version