አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን የመጀመሪያው ችቦ በአዲስ አበባ በይፋ ተለኮሰ።
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴም የኦሎምፒክ ቡድኑ የቶክዮ 2020 የመጀመሪያውን ችቦ በይፋ ለኩሰዋል።
በዚህም ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት “እኛ ኢትዮጵያውያን በተባባረ አንድነትና ህብረት ወደ ላቀ ብልፅግና እንደርሳለን፤ ኢትዮጵያ ብዙ ጀግኖች ታፈራለች” ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለኦሎምፒክ ቡድኑ ድጋፉን በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሳይቷል ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለውርቅ፥ “እኔም ባለኝ አቅም ሁሉ እደግፋለሁ” ነው ያሉት።
በዓለም መድረክ ላይ ሰንደቅ ዓላማችንን ከማውለብለብ ባሻገር ያስለመዳችሁንን እንድታጎናፅፉን እንፈልጋለን ከዛሬዋ ቀን ጀምሮ በርትታችሁ ስሩም ብለዋል።
በስነስርዓቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ ስፖርተኞች ታዋቂ ሰዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የቀጣይ የችቦ ልኮሳን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መረከቡን ከአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ያኘነው መረጃ ያመለክታል።