የሀገር ውስጥ ዜና

የምስራቅ ዕዝ የመከላካያ ሰራዊት ቀንን አከበረ

By Tibebu Kebede

February 15, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የምስራቅ ዕዝ ስምንተኛውን የመከላካያ ሰራዊት ቀንን በጽዳት ዘመቻ፣ በደም ልገሳና በፓናል ውይይት በሀረር ከተማ አከበረ።

በዚህ የፓናል ውይይት ላይ የተገኙት የምስራቅ ዕዝ ዋና አዘዥ ሜጀር ጀነራል ዘውዱ በላይ፥ ሰራዊቱ የሚያጋጥሙትን ችግሮች በማለፍ በአገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል።