Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቦርዱ በመራጮች ትምህርትና ምርጫ መታዘብ ዙሪያ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመራጮች ትምህርት እና ምርጫ መታዘብ ዙሪያ ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር እየተወያየ ነው።

የውይይት መድረኩ  መራጮች በምርጫ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ እና በምርጫ መታዘብ ዙሪያ ያለውን ልምድ ለመዳሰስ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

ከዚህ ባለፈም የመራጮች ትምህርት ፍቃድ አሰጣጥና የስነ-ምግባር መመሪያ ላይ የተሰጡ ግብዓቶችን በማስተዋወቅ ውይይት የሚደረግ መሆኑ ነው የተገለጸው።

እንዲሁም በሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ አሰጣጥ፣ አሰራር እና  ስነ-ምግባር መመሪያ ላይ ውይይት የሚደረግ መሆኑን ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በመድረኩ ላይ የሲቪል ማህበራት ተወካዮች የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን ጨምሮ የተለያዩ የቀድሞ ተሞክሮዎቻቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

Exit mobile version