Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ወድቆ ያገኙትን 3 ሺህ 900 ዶላር ያስረከቡት የፖሊስ አባላት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አራት የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ወድቆ ያገኙትን 3 ሺህ 900 የአሜሪካ ዶላር ማስረከባቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ምክትል ኢንስፔክተር ዘነበ እሸቱ ፣ምክትል ኢንስፔክተር ዳግም ግርማ እና ዋና ሳጅን አለምነሽ ግርማ የተባሉ የአቃቂ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አባላት በጥበቃ ስራ ላይ እያሉ ቆሻሻ በተደረገበት ፌስታል ውስጥ የተጠቀለለ 1 ሺህ 900 ዶላር አግኝተው ለአቃቂ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስረክበዋል፡፡

በተመሳሳይም ምክትል ሳጅን ብርቱ ሙዳ በፖሊስ ጣቢያው አካባቢ ስትንቀሳቀስ በማስክ የተጠቀለለ 2 ሺህ የአሜሪካ ዶላር አግኝታ ወዲያውኑ ለፖሊስ ጣቢያው ማስረከቧ ተገልጿል።

አባላቱ በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል ከህዝብና ከመንግስት የተሰጠን አደራ ነው ያሉ ሲሆን÷ በሰሩት አርዓያነት ያለው ተግባር መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ይህ ተግባራቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ዝግጁ ነን ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version