አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የገዳሪፍ ዋና አስተዳዳሪ ሜጀር ጀኔራል ነስረዲን አብዲ ለጉብኝት ጎንደር ገብተዋል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ማስተዋል ስዩም ለአስተዳዳሪው አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሜጀር ጀኔራሉ ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ሀገሬ ውስጥ ያለሁ ያህል ይሰማኛል ብለዋል።
በቆይታቸውም በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በወረታ ደረቅ ወደብ የመጀመሪያ ምዕራፍ ምረቃ ላይ አስተዳዳሪው የሚሳተፉ ይሆናል።
በመርሀ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ተመሥገን ጥሩነህ፣ የክልሉና የፌደራል የሥራ ኃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት የአማራ ክልል የሥራ ኃላፊዎች እና የገዳሪፍ ክፍለ ግዛት ልዑክ የጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ በባሕር ዳር የሚመክሩ ሲሆን፥ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችንም ይጎበኛሉ።
ኢትዮጵያና ሱዳን በአማራ ክልል በተለይም በሱዳኗ ገዳሪፍ ክፍለ ግዛት ሰፊ ወሰንን ይጋራሉ።
የአማራ ክልል እና የገዳሪፍ መሪዎች በድንበር አካባቢ ፀጥታን ለማስከበር፣ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመቆጣጠር እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች በጋራ ለመሥራት በየጊዜው እየተገናኙ ይመክራሉ።
በምናለ አየነው