ስፓርት

በስፔን እና በሜክሲኮ የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

By ዮሐንስ ደርበው

December 13, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ አገራት በተደረጉ የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በስፔን በተደረገ የማላጋ ማራቶን ውድድር በሴቶች÷ አትሌት ፅግነሽ መኮንን አንደኛ፣ ያይንአበባ እጅጉ ሁለተኛ እንዲሁም ማሪቱ ከተማ አምስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡

በሜክሲኮ በተደረገ ጉዋዳላጃራ ማራቶን ውድድር ደግሞ በወንዶች÷ አትሌት ደራራ ደሳለኝ አንደኛ፣ ፀጋዬ ደበላ ስድስተኛ እንዲሁም ሙሳ ባቦ ስምንተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን ጨርሰዋል።

በሴቶች ደግሞ አትሌት አልማዝ ነገደ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

በባህሬን በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች÷ ጀማል ይመር ስድስተኛ፣ ሃፍቱ ተክሉ ስምንተኛ፣ ቦኪ ድሪባ ዘጠነኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩን ማጠናቀቃቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዚሁ ውድድር በሴቶች÷ ጎይቶም ገ/ስላሴ አንደኛ፣ ሃዊ ፈይሳ ስድስተኛ፣ ቦሰና ሙላቴ ስምንተኛ፣ ዳዊት ስዩም ዘጠነኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡