አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በእሁድ ገበያ ከ48 ሚሊየን ብር በላይ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ግብይት መፈጸሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
7ኛ ሳምንቱን በያዘው የእሁድ ገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለህብረተሰቡ ማቅረቡን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡
በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ምርቶችን ለማቅረብ በተመረጡ አምስት ክፍለ ከተሞች የተጀመረው የእሁድ ገበያ÷ የህብረተሰቡን የአቅርቦት ተደራሸነት ጥያቄ መነሻ በማድረግ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች እንዲቀርብ መደረጉን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡
በዚህም ከ48 ሚሊየን ብር በላይ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በማህበራቱ በኩል ግብይት መፈፀሙን ከከተማ አስተዳደሩ ፕረስ ሴክረታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በከተማዋ ሁሉም አካባቢዎች የዋጋ ንረትን ለመቀነስ የገበያ መዳረሻዎችን የማስፋቱ ስራ በቀጣይም በአስተዳደሩ በኩል ተጠናከሮ ይቀጥላል ነው የተባለው፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡