አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥቅምት ወር ከወጪ ንግድ 311 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከጥቅምት ወር ወጪ ንግድ 358 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 311 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጿል፡፡
አፈጻጸሙም 86 ነጥብ 80 በመቶ መሆኑን ነው ከሚኒስቴሩ ያኘነው መረጃ ያመላከተው፡፡
የግብርናው ዘርፍ 205 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ገቢ በማስገኘት ትልቁን ድርሻ የያዘ ሲሆን÷ የኢንዱስትሪ ዘርፍ 39 ነጥብ 6 ሚሊየን፣ የማዕድን ዘርፍ 58 ነጥብ 5 ሚሊየን እንዲሁም ከኤሌክትሪክና ሌሎች 7 ነጥብ 54 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉ ተመላክቷል፡፡
የወጪ ንግድ ገቢውን ለማሳደግ አምስት ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ ምርት ገበያ ግብይት ሥርዓት እንዲሁም ሰባት የምርት አይነቶችን ደግሞ ወደ ውል አስተዳደር ሥርዓት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!