ማንቸስተር ዩናትድ አርሴናልን 3 ለ 2 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ትላንት ምሽት በተካሄደው የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናትድ አርሴናልን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡
የማንቸስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ጎሎች ቡሩኖ ፈርናንዴዝ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሲያስቆጥሩ÷ የአርሴናልን ሁለት ጎሎች ስሚዝ ሮዉ እና ማርቲን ኦዲጋርድ አስቆጥረዋል፡፡
ማንቸስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ሶስት ደረጃዎችን በማሻሻል ሰባተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷አርሴናል አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ የነጥብ ልዩነታቸዉም ወደ ሁለት መጥበብ ችሏል፡፡
በሌላ የእንግሊዝ ፕሪሜሪሊግ ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ብሬንት ፎርድን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ጎሎችን ካኖስ በራሱ መረብ ላይ ሲያስቆጥር ሰን ሁዊንግ ሚን ሁለተኛዉን ጎል አስቆጥሯል፡፡