አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለግብርና ምርት አቀነባባሪ ኢንዱስትሪዎች ግብዓት እንዲያገኙ ባስቻለው ልዩ የግብይት መስኮት አገልግሎት በአንድ ዓመት 48 ሺህ ቶን አኩሪ አተር በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር አገበያይቷል፡፡
የልዩ መስኮቱ ግብይት የዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቀጥተኛ ተገበያይ ሆነውና በግብይት ሥርዓቱ አሠራርና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ስልጠና ተሰጥቷቸው በግብዓትነት የሚጠቀሙበትን የጥራት ደረጃ በላቦራቶሪ የተረጋገጠ ምርት በኤሌክትሮኒክ ግብይት አማካይነት የሚገዙበት ስርዓት ነው፡፡
ይህም በዓመታዊ የምርት መጠናቸው ልክ የሚያስፈልጋቸውን ግብዓት እንዲገዙ ማስቻሉን ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡