አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ዛሬ በሚካሄደው 14ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሴናል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች የ 5 ነጥብ ልዩነት ያላቸዉ ሲሆን÷ በጨዋታዉ የማይክል አርቴታ ቡድን የሚያሸነፍ ከሆነ ከቀያዮቹ ሰይጣኖች በ8 ነጥብ ይርቃል፤ ማንቸስተር ዩናይትድ የሚያሸንፍ ከሆነ ደግሞ የነጥብ ልዩነታቸዉ ወደ 2 የሚጠብ ይሆናል።
በማንቸስተር ዩናይትድ በኩል አምበሉ ሃሪ ማጉዌር ከቅጣት መልስ በጨዋታዉ የሚሰለፍ ሲሆን÷ የመሀል ተከላካዩ ራፋኤል ቫራን ከጨዋታው ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል።
በአርሴናል በኩል ቡካዮ ሳካ ከጨዋታው ውጭ የመሆን እድል ሲኖረው÷ ግራናይት ዣካ እና ተከላካዩ ሴድ ኮላሲናክ ከጨዋታዉ ውጭ መሆናቸዉ ተረጋግጧል፡፡
በዉጤት ቀዉስ ዉሰጥ የሚገኙት ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት ላይ በኦልትራፎርድ ስታዲየም ጨዋታቸዉን ያደርጋሉ ሲል ሰካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡
በሚኪያስ አየለ