የሩሲያ የቀድሞው የማረሚያ ቤት ሀላፊ ፍርድ ቤት ውስጥ ራሱን አጠፋ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሩሲያ የቀድሞው የማረሚያ ቤት አገልግሎት ሃላፊ ፍርድ ቤት ውስጥ ራሱን ማጥፋቱ ተነግሯል።
ቪክቶር ስቪሪዶቭ የተባለው ግለሰብ የሩሲያ ማረሚያ ቤት አገልግሎት የሞተር ትራንስፖርት ክፍል ሃላፊ ሆኖ በሚያገለግልበት ወቅት 125 ሺህ ዶላር ከምክትል ዳይሬክተሩ ተቀብሏል በሚል ተከሶ ጥፋተኛ ተብሏል።
ይህን ተከትሎም በተላለፈበት የሶስት ዓመት የእስር ቅጣት ፍርድ ቤት ውስጥ ራሱን አጥፍቷል።
የፍርድ ቤቱ ዳኛ ግለሰቡ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወሰድ ትዕዛዝ ባስተላለፉበት ቅፅበት ግለሰቡ በግንባሩ ላይ በመተኮስ ራሱን ማጥፋቱ ተገልጿል።
የፍርድ ቤቱ ቃል አቀባይ ራሱ ያጠፋበትን የጦር መሳሪያ ወደ ፍርድ ቤት ይዞ ሳይመጣ አይቀርም ብለዋል።
ፖሊስም ግለሰቡ ራሱን ማጥፋቱን ተከትሎ በፍርድ ቤቱ የፀጥታ አካላት ላይ ምርምራ መጀመሩ ተጠቁሟል።
የካንሰር ህመምተኛ እንደሆነ የተነገረው ግለሰብ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት በቤት ውስጥ እስር ላይ እንደነበረ ነው የተነገረው።
ምንጭ፡- ቢቢሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision