Fana: At a Speed of Life!

በሳይበር ምህዳር ደህንነት ላይ ያተኮረ የበይነ መረብ ስልጣኔ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳይበር ምህዳር ደህንነት እና ዝማኔ ላይ ትኩረት ያደረገ የመጀመሪያው የቻይና የበይነ መረብ ስልጣኔ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡
በቤጂንግ እየተካሄደ ባለው ኮንፈረንስ በቀረበውና በቻይናው ፕሬዚደንት ቺ ጂንፒንግ የተላከው መልዕክት፤ አዎንታዊ ኃይልን እና ጥንካሬን በመጠቀም የተሻለ የሳይበር ምህዳር ለመፍጠር የጋራ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ፕሬዚደንቱ በይነ መረብ የማህበራዊ ስልጣኔ አካል መሆኑን ጠቅሰው÷ የሳይበር ምህዳር አስተዳደርን የበለጠ ለማጎልበት እና የበይነ መረብ ግንባታን ለማስተዋወቅ በትኩረት እንዲሰራም ጠይቀዋል፡፡
ኮንፈረንሱ እየተካሄደ ያለው “የበይነ መረብ ሥልጣኔን በጋራ እንገንባ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲሆን÷ በሳይበር ምህዳር ደህንነት እና በበይነ መረብ ስልጣኔ ምክክር ሲደረግ በሀገሪቱ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡
የዘርፉ ባለሙያዎች፥ መንግሥታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተሻለ የሳይበር ምህዳር ለመፍጠር ከመንግስታት ጋር በጋራ ሊሰሩ ይገባልም ነው የተባለው፡፡
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የበይነ መረብ ስልጣኔን በመገንባት ሂደት አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
በየሻምበል ምህረት
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.