Fana: At a Speed of Life!

አካባቢያችንን ከመጠበቅ ባለፈ ወደ ግንባር በመዝመት ኢትዮጵያን ለመታደግ ዝግጁ ነን-የምዕራብ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 07፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን በጊንቢ ከተማ አሸባሪው ህወሓት እና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ።
በሰልፉም ላይ የተሳተፉ የዞኑ ነዋሪዎች አሸባሪዎቹ አገርን ለማፍረስ እያደረጉት ያለውን የሽብር ተግባር አውግዘዋል።
ሰልፈኞቹ “መራር ትግል አካሂደንና ልጆቻችንን ገብረን እንደ ህዝብ ያገኘነውን ድል ዳግም ሊነጥቀንና ሊጨቁነን የሚመጣን የትኛውንም አካል አንታገስም” ብለዋል።
በመራር ትግል የተገኘውን ለውጥ አሳልፈን አንሰጥም፣ ጠላታችን አሸባሪው ህውሓትና ተላላኪው ሸኔን ለማጥፋትና ኢትዮጵያን ለመታደግ እንዘምታለን ሲሉም ሰልፈኞቹ በያዟቸው መፈክሮች አስተጋብተዋል።
አካባቢያችንን በንቃት ከመጠበቅም ባለፈ የህልውና ዘመቻውን በመደገፍና ወደ ግንባር በመዝመት ኢትዮጵያን ለመታደግ ዝግጁ መሆናቸውንም ነው ሰልፈኞቹ የተናገሩት።
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ታምሩ በሰልፉ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት፥ በህዝብ የተገኘው ለውጥና የተመዘገበው ድል በአሸባሪው ህውሓትና ሸኔ የማይቀለበስ ነው ብለዋል።
በህዝብ ትግል የተገኘን ድል በሁለቱ አሸባሪዎች እንደማይቀለበስ የተናገሩት አቶ ሰለሞን ፥ እነዚህ ቡድኖች የውጭ አገራት ተልዕኮን በመያዝ አገር ለማፍረስና ህዝብን ወደ ዳግም ጭቆና ለመመለስ እያደረጉት ያለውን የሽብር ተግባር የዞኑ ህዝብ በአንድነት በመመከት ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና እናሸጋግራታለን ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People reached
217
Engagements
Boost post
565
23 Comments
16 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.