Fana: At a Speed of Life!

የመሬት ወረራ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተና እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ

የመሬት ወረራ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተና እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመሬት ወረራ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተና እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ።

የፌዴራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን ብልሹ አሰራር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች ፣የሚመለከታቸው አካላት እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በውይይት መድረኩ ላይ እየተሳተፉ ነው።

በመድረኩ ላይም በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለው የመሬት ወረራ ለከተማው አስተዳደር ፈተና እየሆነ መምጣቱ ተነስቷል።

ሙስናና ብልሹ አሰራር፣ የመረጃ አያያዝ ማነስ፣ የግልጽነትና ተጠያቂነት ችግሮች ከህግ ስርአቶች አለመከበር ጋር ተዳምረው ለመሬት ወረራው መስፋፋት ምክንያት ሆነዋል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማት ቢሮም፥ በከተማዋ ህገወጥ የመሬት ወረራ እና ተያያዥ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል እና አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓቱን የማዘመን ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጿል ።

በቀጣይ ችግሩን ለመቅረፍ በቂ በሚባል ደረጃ የማስተካከያ እርምጃ ለምን መውሰድ አልተቻለም በሚል ርእሰ ጉዳይ ላይም ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት በአዲስ አበባ ደረጃ ችግሩን ለመፍታት ምን መደረግ አለበት በሚለው ላይም እየተወያዩ ነው።

በተስፋዬ ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.