ከአሸባሪ ቡድኖች ጋር ግንኙነት የነበራቸው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚከለክላቸው ተግባራት በመሳተፍና ከአሸባሪ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ፈጥረው ለጠላት እገዛ በማድረግ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።
ከተጠረጠሩ ግለሰቦች መካከል÷ የሀገር መከላከያ አመራር የነበሩና በሀገር ላይ ክህደት ፈፅመው ተሸሽገው የቆዩ እንዳሉበት የቢሮው ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ተናግረዋል፡፡
ከሰሞኑ አዲስ አበባ ላይ እየተካሄደ ያለውን አሰሳና ፍተሻ በመሽሽ ሀዋሳ ውስጥ ቤት ተከራይተው ተሸሽገው የነበሩና የተለያዩ የባንክ ሒሳብ ደብተሮች የያዙ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል ይገኙበታልም ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያን ከተደቀነባት የህልውና አደጋ በአጭር ጊዜ ለማላቀቅ በሀገር ደረጃ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዜጎች ተፈጻሚ ሊያደርጉት እንደሚገባ ኃላፊው አሳስበዋል፡፡
በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚከለክላቸው እኩይ ተግባራት ላይ በመሳተፍ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኃላፊው አስታውቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!