ሬውተርስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን አስመልክቶ ያወጣው ዘገባ ፍጹም ስሕተት ነው – መንግስት ኮሙዩኒኬሽን
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሬውተርስ በኢትዮጵያ የጸደቀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስመልክቶ ያወጣው ዘገባ ፍጹም ስሕተት መሆኑን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አስታወቀ።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዜጎች ከመታወቂያ ባሻገር እንደ መንጃ ፈቃድ፣ የሥራ ቦታ መታወቂያ እና ፓስፖርትን አልያም ሌላ ማንነትን የሚገልጽ ማንኛውንም ሕጋዊ ሰነድ እንዲጠቀሙ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡
ሬውተርስ ግን መታወቂያ ብቻ መያዝ ግዴታ ነው በሚል ያሠራጨው ዘገባ ስሕተት መሆኑን ከአዋጁ በመነሣት መገንዘብ ይቻላል ብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሕወሓት ሲተገብረው የነበረውን የብሔር ማንነትን የሚገልጸውን የመታወቂያ ካርድ ለመተካት እየሠራች መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን