የህልውና ዘመቻውን የሚደግፍና ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰልፍ በዲሲ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የህልውና ዘመቻ የሚደግፍና የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ ተካሂዷል።
ሰላማዊ ሰልፉ “በሃገር ህልውና እና አንድነት አንደራደርም” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው።
በነጩ ቤተ መንግስት ፊት ለፊት በተካሄደው በዚህ ሰልፍ አሜሪካ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አክብሪ፣ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ጣልቃ ገብነት ታቁም፣ ኢትዮጵያ በራሷ ጉዳይ የሌሎችን ትዕዛዝ አትቀበልም፣ “ኢትዮጵያን ከአጎዋ የማስወጣት ውሳኔ ስህተት ነው፤ የሚጎዳው ንጹሃን ዜጎችን ነው የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡
በተጨማሪም ኢትዮጵያ አሸናፊ የሆነችው በአጎዋ ሳይሆን በአድዋ ነው፣ ሲ ኤንኤን በኢትዮጵያ ላይ የሚሰራውን ሀሰተኛ መረጃ ያቁም፣ ኢትዮጵያ ቅኝ ገዢዎችን አሸንፋለች አሁን ኒዮ-ኮሎኒያሊስቶችንም ታሸንፋለች” የሚሉ ሃሳቦች ተስተጋብተዋል።
በሰልፉ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶችና ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እየተሳተፉ ሲሆን÷ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ህወሓት በፈጸመው ጥቃት በግፍ
የተጨፈጨፉ የሃገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አባላት የሚዘከሩበት መርሃ ግብርም ተካሂዷል።
ሠልፈኞቹ የሃገርን ሕልውና ለማስጠበቅ መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ለሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ሌሎች የጸጥታ አካላት አጋርነታቸውንና ድጋፋቸውን አሳይተዋል።
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ያልተገባ ጫና እና ጣልቃ ገብነት እንድታቆምና የተሳሳተ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋን እንድታጤን የሚያሳስቡ መልዕክቶችም ተላልፈዋል።
ሰላማዊ ሠልፍን በሠላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ግብረ ሃይል በዲሲ እና በሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና የተለያዩ ተቋማት ትብብር የተዘጋጀ መሆኑን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!