የጎንደር ከተማ አመራሮች አሸባሪው ቡድንን ለመፋለም ወደ ግንባር ዘመቱ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የክልሉ መንግስት ባቀረበው የክተት አዋጅ መሰረት አመራሩ በግንባር ህዝቡን በማስተባበር እየዘመተ መሆኑን የጎንደር ከተማ አስተዳደርሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩ አቡሃይ ገልፀዋል።
በእስከ አሁኑ ሂደት አንድ ብርጌድ የከተማው አመራር ወደ ግንባር መዝመቱን የተናገሩት ምክትል ከንቲባው፥ አመራሩ ከህዝቡ በፊት ራሱን አስቀድሞ ወራሪውን ሀይል እየተፋለመ ነው ብለዋል።
እኔ ልቅደም የሚል የመዝመት ተነሳሽነት በአመራሩ ታይቷል ያሉት አቶ ባዩ ፥ቀሪው የከተማው አመራር ደግሞ የከተማዋን ሰላም በማስጠበቅና ስንቅ እንዲዘጋጅ በማስተባበር ሀላፊነቱን እየተወጣ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ወራሪ እና አሻባሪው የህውሓት ሀይል ለመፋለም በቁርጠኝነት መነሳታቸውን የገለፁት ደግሞ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የከንቲባው የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪው አቶ አዝመራው ተዘራ ናቸው።
ከሚመቸው ተሽከርካሪና ከወንበሮቻችን ወርደን የጠላት ሀይል መመከት የምርጫ ጉዳይ አይደለም ያሉት አቶ አዝመራው፥ ሁሉም የከተማው አመራር በተሰጠው ተልዕኮ ግዳጁን እየተወጣ ነው ብለዋል።
ብቸኛው አማራጭ ማሸነፍ ነው ያሉት አማካሪው ወራሪውን ሀይል ለመደምሰስ በቁጭት አመራሩ መነሳቱን ገልፀዋል።
በቀጣይም የከተማው አመራር በግንባር በመዝመት የኢትዮጵያን ጠላት ድባቅ ለመምታት ተሳትፎውን ይቀጥላል ብለዋል ሀላፊዎቹ።
በምናለ አየነው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!