Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ ለሰራዊቱ ስንቅ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ለሰራዊቱ ስንቅ በማዘጋጀት የኋላ ደጀንነት ሚናቸውን እየተወጡ ነው፡፡

በፋሲል እና ጃንተከል ክፍለ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞች የኋላ ደጀንነት ሚናቸውን ለመወጣት ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይል፣ ለፋኖ እና ለአማራ ሚሊሻ የደረቅ ሬሽን ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

የስንቅ ዝግጅቱ በሴት ሊግ እና በማህበላዊ ዘርፍ የሚመራ ሲሆን በክፍለ ከተማው ስር በሚገኙ ቀበሌዎች የበጎ ፈቃደኛ ሴት አደረጃጀቶች ተግባሩ እየተከናወነ ይገኛል ፡፡

ህይወቱን ያለ ስስት እየሰጠን ለማገኘው ሰራዊታችን የደረቅ ሬሽን በማዘጋጀት የደጀንነት ሚናቸውን እየተወጡ እንደሆነም ነዋሪዎቹ መናገራቸውን ከጎንደር ኮሚኒኬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.