Fana: At a Speed of Life!

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ህብረብሔራዊነትን በሚያጠናክር መልኩ እንደሚከበር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ህዳር 29 በተለያየ መረሐ ግብር በድሬዳዋ ከተማ እንደሚካሄድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡
በዓሉ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ሕብረብሔራዊ አንድነት እንደሚጠናክር ጠቁመው÷ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ መሠረት የሚጥል በዓል ይሆናልም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ከዚህ በፊት የነበረው የአንድነታቸው ግርማ ሞገስ ለውጭ ወራሪዎችም ሆነ ለውስጥ ባንዳዎች ትልቅ ራስምታት ሆኖ መሰንበቱን ያስታወሱት አፈ-ጉባዔው÷ የዘንድሮው የህዳር 29 በዓል አከባበርም ይህንን ዓላማ የሚያስጠብቅ ይሆናል ማለታቸውን ከፌዴሬሽን ምክርቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.