Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወንድም ካሊድ ምግባረ ሰናይ ፋውንዴሽን በመገኘት ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ 1 ሺህ 496ኛውን የመውሊድ በዓል ምክንያት በማድረግ የወንድም ካሊድ የበጎ አድራጎት ፋውንዴሽን ለሚረዳቸው የጎዳና ተዳዳሪዎች ማዕድ አጋርተዋል።

በአዲስ አበባ በሚገኘው የወንድም ካሊድ የበጎ አድራጎት ፋውንዴሽን እየተካሄደ በሚገኘው መርሃ ግብር÷ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ እና ሌሎችም እንግዶች ታድመዋል።

ፕሬዚደንቷ በፋውንዴሽኑ በመገኘት ከ100 በላይ ለሆኑ በፋውንዴሽኑ ለሚገኙ እና ከጎዳና ተነስተው በስልጠና ላይ ለሚገኙ ወገኖች ነው ማዕድ ያጋሩት።

በተጨማሪም ፕሬዚደንቷ ለሌሎች ከ100 በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ቤታቸው ወስደው የሚጠቀሙባቸው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

የአዲስ አበባ አስተዳደር በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለፋውንዴሽኑ 20 በጎችን ድጋፍ ማድረጉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመርሃ ግብሩ ላይ ተናግረዋል።

ወንድም ካሊድ የበጎ አድራጎት ፋውንዴሽን በተቋቋመ በአንድ ዓመት ጊዜ ከ1 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ለቁም ነገር ማብቃቱም ኢዜአ ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.