የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝበ ሙስሊሙ ለአገራዊ ለአንድነት ሉአላዊነት እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነት እና እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥሪ አቅርቧል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1496ኛው የነብዩ መሐመድ መውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ።
ምክር ቤቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ፥ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የነብዩን መንገድና አስተምህሮ በመከተል ያጡና የተቸገሩ ወጎኖችን በመደገፍና በማገዝ ሊሆን ይገባል ነው ያለው።
ሕዝበ ሙስሊሙ ለአንድነቱና ሉአላዊነቱ እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት እና እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።
“ባለንበት በአዲስ ምዕራፍ እንደ አባቶቻችን ሁሉ የራሳችንን ደማቅ ታሪክ ልንፅፍ ይገባል” ያለው የምክር ቤቱ መግለጫ ፥ “ይህ የሚሆነውም ጀግኖች አባቶቻችን በደምና በአጥንታቸው በከፈሉት መስዋዕትነት አንድነቷነና ሉዓላዊነቷን አስጠብቀው ያስረከቡንን አገር እኛም እንደነሱ ወቅቱ የሚጠይቀው አስፈላጊውን ትግል በማድረግና መስዋዕትነት በክፈል ታፍራና ተከብራ የቆየች ኢትዮጵያን ማስቀጠል ስንችል ነው” ብሏል ምክር ቤቱ በመግለጫው።
ኢትዮጵያ የበለፀገችና እውነተኛ ዴሞክራሲ የሚተገበርባት እንድትሆን ሁሉም በያለበት መስክ የበኩሉን እንዲወጣም ምክር ቤቱ መልዕክት አስተላልፏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
71
Engagements
–
Distribution Score
Boost Post
69
1 Share
Like
Comment
Share