የቦብ ማርሌይ ልጅ ጁሊያን ማርሌይ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ለማድረግ አዲስ አበባ ገባ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ)የታዋቂዉ ሬጌ አቀንቃኝ ቦብ ማርሌይ ልጅ ጁሊያን ማርሌይ እና የሙዚቃ ጓደኞቹ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
የሁለት ጊዜ የግራሚ አዋርድ እጩ እና የሬጌ ንጉሱ ቦብ ማርሌይ ልጅ ጁሊያን ማርሌይ እና ጓደኞቹ በሳምንቱ መጨረሻ በጊዮን ሆቴል የሬጌ ኮንሰርት እንደሚያዘጋጁ አስታዉቀዋል፡፡
የሙዚቃ ኮንሰርቱ ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ ሰላም መሆኗን ለአለም አቀፉ ማህበረሰቡ በማስተዋወቅ የቱሪዝም እንቅስቃሴው እንዲያንሰራራ ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል።
ዝነኞቹን አቀንቃኞች ቱሪዝም ኢትዮጵያ ከአይዞን ፋዉንዴሽን ጋር በመተባበር ባደረገላቸዉ ግብዣ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸዉን ከቱሪዝም ኢትዮጵያ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like
Comment
Share