Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ  ከቻይና  አምባሳደር ዛሆ ዛይሁዋንና ከቻይና የኢኮኖሚ እና የንግድ ጉዳዮች ሚኒስተር ኮንስላር ሩ ያንግ ዪ ሃንግ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይቱ በሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ የኢንቨስትመንት ግንኙነት በፕሮሞሽን፣ በአፍተር ኬር ፕሮግራም እንዲሁም በተለያዩ የልምድ ልውውጦች ማጠንከር፣ ከቻይና ባለሃብቶች ጋር ተደጋጋሚ የትስስር መድረኮችን በመፍጠር ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

እንዲሁም በኢንቨስትመንቱ ሴክተር አብሮ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ለመፈራረምም ከስምምነት ላይ መደረሱን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.