Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሚኒስትርነት የቀረቡለትን ዕጩዎች አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቀረበለትን ዕጩ ሚኒስትሮችን ሹመት በሁለት ተቃውሞ እና በ12 ድምጸ ተአቅቦ አጸደቀ፡፡
በዚሁ መሠረት የሚከተሉት ሚኒስትሮች ሹመታቸው ጸድቋል፡፡
1. አቶ ደመቀ መኮንን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር
2. ዶክተር አብርሃም በላይ – የመከላከያ ሚኒስትር
3. አቶ ዑመር ሑሴን – የግብርና ሚኒስትር
4. አቶ መላኩ አለበል – የኢንዱሰትሪ ሚኒስትር
5. አቶ ገብረመስቀል ጫላ- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
6. ኢንጂነር ታከለ ኡማ- የማዕድን ሚኒስትር
7. አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ- የቱሪዝም ሚኒስትር
8. ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
9. አቶ አሕመድ ሽዴ – የገንዘብ ሚኒስትር
10. አቶ ላቀ አያሌው -የገቢዎች ሚኒስትር
11. ዶክተር ፍጹም አሰፋ – የፕላንና ልማት ሚኒስትር
12. ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ -የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
13. ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ- የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር
14. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ኢብራሂም- የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር
15. ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ- የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር
16. ኢንጂነር አይሻ መሐመድ- የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
17. ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ- የትምህርት ሚኒስትር
18. ዶክተር ሊያ ታደሰ- የጤና ሚኒስትር
19. ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ- የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
20. አቶ ቀጀላ መርዳሳ-የባህልና ስፖርት ሚኒስትር
21. ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ-የፍትህ ሚኒስትር
22. አቶ ብናልፍ አንዱዓለም – የሰላም ሚኒስትር፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.