Fana: At a Speed of Life!

የንፋስ መውጫ ነዋሪዎች በግንባር በመገኘት ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት የምሳ ግብዣ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋይንት ንፋስ መውጫ ቀበሌ 02 ነዋሪዎች በግንባር በመገኘት ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት የምሳ ግብዣ አድርገዋል።
ግፍ እና በደል የፈፀመባቸውን ወራሪ ሃይል ሙሉ በሙሉ እስኪ ደመሰስ ድረስ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን ያላቸውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በቀበሌው የመንግስት ሰራተኛ አቶ ፃዲቅ ገነነ ተናግረዋል።
መከላከያ ሰራዊታችን በሚያደርገው ተጋድሎ የበለጠ እንድንተማመንበት አድርጎናል ያሉት አቶ ፃዲቅ ገነነ ፥ አይደለም በቦታው ተገኝቶ ምግብ አብስሎ መመገብ ይቅርና በሌሎችም ተግባራት አጋርነታችንን በተግባር እናረጋግጣለን ብለዋል።
በግንባሩ የሚገኝ አንድ አሀድ አዛዥ ሌ/ኮ ሁሴን እንድሪስ እንደተናገሩት ፥የጋይንት ንፋስ መውጫ ቀበሌ 02 ነዋሪዎች ለሰራዊቱ ላደረጉት የምሳ ግብዣ በመከላከያ ስም አመስግነዋል።
ወርቃማ ደጀን ይዘን የሽብርተኛውን ሃይል ሙሉ በሙሉ እንደመስሰዋለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.