ሩሲያ በክህደት የጠረጠረችውን የመረጃ ደህንነት ከፍተኛ ኃላፊ አሰረች
አዲስ አበባ፣ መሰከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ)ሩሲያ በክህደት የጠረጠረችውንና ከሀገሪቱ የደህንነት ተቋማት አንዱ የሆነውን የመረጃ ግሩፕ-ኣይ ቢ ኃላፊ አሰረች፡፡
የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንጀሉ የተጠረጠረውን ከፍተኛ የመረጃ ደህንነትኃላፊ ኢልያ ሳችኮቭን ለሁለት ወራት በእሰር እንዲቆይ ያዘዘ ቢሆንም÷ በክሶቹ ዝርዝር ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡
ይሁን እንጅ የ35 ዓመቱ ኢልያ ሳችኮቭ የሩስያ ሚስጥራዊ ሰነዶች ለውጭ አሳልፎ ሰጥቷል በሚል ሳይከሰስ እንዳልቀረ ከምንጮቼ ሰምቻለሁ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሳችኮቭ የሚመራው የግሩፕ-አይ ቢ ተቋም የመረጃ ጥቃትን በመከላከል የሚሰራ ሲሆን÷ እንደ ኢንተርፖል የመሳሰሉ ትላልቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት ደምበኞቹ ናቸው፡፡
ተጠርጣሪው ወንጀለኛ ሆኖ ከተገኘ በሩስያ ህግ መሰረት እስከ 20 ዓመት የእስር ቅጣት የሚበየንበት ይሆናል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!