የደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ዞኖች አመራሮች በጋይንት ግንባር የመስቀል በዓልን አከበሩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ጎንደር ዞን እና ሰሜን ወሎ ዞን አመራሮች በግዳጅ ከሚገኙ የሰራዊት አባላት ጋር በጋይንት ግንባር የመስቀል በዓልን አከበሩ፡፡
ከመከላከያ ሰራዊቱ፣ ከልዩ ሀይል አባላት፣ ከፋኖ እና ሚሊሻ ጋር በመሆን ነው በዓሉን በጋይት ግንባር በመሀኘት አመራሮቹ ያከበሩት፡፡
በዱር በገደሉ እየተዋደቁ የሚገኙትን የሰራዊት አባላቱን የህዝብ ደጀንነት ለማሳየት የመስቀል በዓልን በጋራ ለማክበር በማሰብ ተገኝተናል ያሉት የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ ናቸው።
የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጋሻው አስማማው በበኩላቸው÷ የመስቀል በዓልን ስናከብር በችግር ላይ የሚገኙትን የወሎ እና አካባቢው ህዝብን እያሰብን ነው ብለዋል፡፡
ሰራዊቱም በአጭር ጊዜ ውስጥ ህዝቡን ነፃ እንደሚያደረገው ሙሉ እምነታችን መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በግምባሩ የሚገኙ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችም÷ በግዳጅ ለሚገኙ ሰራዊት የህዝቡ ደጀንነት ወደር የለውም፤ አሁን ከፊታችን ያለውን ጠላት እንደመስሳለን ለዚህ ደግሞ ሀሉም የሰራዊት አባላት በጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።
በምንይችል አዘዘው (ከጋይንት ግንባር)
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!