Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና የሩስያ ትብብር ወደ ላቀ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ነው – አምባሳደር ዩቭጋኒ ቴራኺን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና የሩስያ ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደ ላቀ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ዩቭጋኒ ቴራኺን ተናገሩ፡፡
ሩስያ እና ኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች የደረሱባቸውን ስምምነቶች ወደ ተግባር በመለወጥ ዘርፈ ብዙ ትብብራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሏቸውን ተግባራት በማከናወን ላይ መሆናቸውን አምባሳደር ዩቭጋኒ ቴራኺን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ የገለጹት፡፡
ኢትዮጵያ አሁን የገጠሟትን ችግሮች በድል እንደምትወጣ በፅኑ ሩሲያ እንደምታምን የተናገሩት አምባሳደሩ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስኮች የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የጀመረችውን ጥረት አገራቸው እንደምትደግፍ ተናግረዋል፡፡
አገራቸው በአህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ መድረኮች ላይ ለኢትዮጵያ እያሳየች ያለውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል የተናገሩት አምባሳደሩ፤ ሁለቱ ሀገራት በሰላማዊ የኒውክለር ልማት ዘርፍ የፈፀሙት ስምምነት ወደ ላቀ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል ብለዋል፡፡
በወንድዎሰን አረጋኽኝ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.