አቶ ወርቁ አይተነው ከጎንደር ከተማ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው ከጎንደር ከተማ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
የህብረተሰብ ተወካዮቹ ባለሀብቱ በወቅታዊ የህልውና ዘመቻ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በተመለከተ ምስጋና አቅርበዋል።
ጎንደር ከተማ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ በመጠቀም አቶ ወርቁ አይተነው እንዲያለሙም ጠይቀዋል።
በሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች ከፍተኛ ሀብት ኢንቨስት በማድረግ የተለያዩ ፋብሪካዎችን በመገንባት ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠር መቻላቸውን ያስታወሱት ተሳታፊዎቹ ይህን በጎንደር ከተማ ሊደግሙት ይገባል ብለዋል።
ጎንደርን ለማሳፈር የመጣው የሽብር ቡድን አፍሮ ተመልሷል ያሉት የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ ከተማዋ ለኢንቨስትመንት ምቹ በመሆኗ ባለሀብቱ እንዲያለሙ ጥሪ አቅርበዋል።
ከተማዋን በርካታ ባለሀብቶች ምርጫቸው እያደረጓት ነው ያሉት ከንቲባው ይህን ዕድል ሌሎች ባለሀብቶች እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በበኩላቸው ÷ በከተማዋ ለወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር ይገባል ብለዋል።
ፋብሪካዎቹን ለመንባት ፀጋውን መለየት ያሻል ያሉት አቶ ወርቁ አይተነው በጎንደር ከተማ ፋብሪካዎቹ በጥናት እንደሚገነቡ ተናግረዋል፡፡
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!