ኢትዮጵያ የያዘችውን እውነት ለዓለም ማስረዳት የሁላችንም ኃላፊነት ነው – ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12/2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ ይበልጥ አንድነታችን የሚጠናከርበት ጊዜው አሁን ነው ሲሉ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ተናገሩ፡፡
የሚኒስቴሩ እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች “ የነጭ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት” ዘመቻን ተቀላቅለዋል።
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ “የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ ይበልጥ አንድነታችን የሚጠናከርበት ጊዜው አሁን ነው” ብለዋል።
የኢትዮጵያን አንድነት በማስጠበቅና በሚነዙ አሉባልታዎች ባለመደናገር ጫናዎችን ለመመከት በጋራ መቆም እንደሚገባም ነው የተናገሩት፡፡
ኢትዮጵያ የያዘችውን እውነታ ለመላው ዓለም ማስረዳትም የሁላችንም ሃላፊነት ነው ብለዋል።
በተመሳሳይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማትም የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ዘመቻ መቀላቀላቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው ልክ እንደ አድዋ ሁሉ ለኢትዮጵያ ህልውና በጋራ ትግል የምናደርግበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
ዜጎች በዚህ ዘመቻ ላይ በመቀላቀል የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡም ጥሪ ማቅረባቸዉን ከሚኒስቴሩ ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
“የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት” ንቅናቄ ከመስከረም 3 እስከ 15 ቀን 2014 ዓ.ም እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በተመሳሳይ የነጩ ፖስታ ጎርፍ ለነጩ ቤተ መንግስት ሀገራዊ ንቅናቄን የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ መስሪያ ቤቶች አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ተጀምሯል፡፡
በንቅናቄው ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ እንደገለጹት÷ የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት ንቅናቄ አላማ የኢትዮጵያያን እውነታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ ነው ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!