የኡዋ ወረዳ ከአሸባሪው ህወሓት ነጻ ወጣች
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈንቲ ረሱ ያሎ ድንገተኛ ወረራ በማካሄድ ንፁሀንን በመጨፍጨፍ ወደ አፋር ክልል ሰርጎ የገባው የሽብር ቡድኑ ሰብዓዊና ቁሳዊ ክስረት ገጥሞት ተባሯል፡፡
ህዝብ ውስጥ መሽጎ የቆየው ቡድኑ÷ በዛሬው ዕለት መከላከያ ሰራዊት፣ የአፋር ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ህዝባዊ ሰራዊት ትብብር ከኡዋ ወረዳ ሙሉ በሙሉ በማስወጣት ወረዳውን ነጻ ማድረግ ተችሏል፡፡
ህወሓት ለአፋር ህዝብ ያነሰ ግምት ይዞ ቢነሳም÷ ወረራ ባካሄደባቸው ሁሉም ግንባሮች ከባድ የሆነ ሽንፈትና ትልቅ ኪሳራ ገጥሞታል ነው የተባለው፡፡፡
የአፋር ህዘብና መንግስት አሁንም ቢሆን ወራሪውን ኃይል ሙሉ በሙሉ ከክልሉ ጠራርጎ ለማስወጣት ጥበብ በተሞላበት መልኩ ትግሉን እንደሚቀጥል የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡