Fana: At a Speed of Life!

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 132 ተማሪዎች አስመረቀ

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 132 ተማሪዎችን አስመረቀ።

ከተመራቂዎቹ ውስጥም ወንድ 654 ሴት 478 ተማሪዎች ሲሆኑ በአሁኑ ሰዓት ከሰባት ሺ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።

ዮኒቨርሲቲው ከተመሠረተ አራት አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የዛሬው የተማሪዎች ምርቃት ለሁለተኛ ዙር መሆኑ ታውቋል።

የዮኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶር ኢንጂነር ቶፊቅ ጀማል ባደረጉት ንግግር ተመራቂ ተማሪዎች ለሀገራቸው ለውጥና እድገት ጠንቅረው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ተቋሙ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ላይ የተለያዩ ተግባራቶችን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል።

በሀገሪቱ የተከሰተው ጫና ያነሱት ፕሬዚዳንቱ አንድነትን በማጠናከር ይህን ጊዜ መሻገር ይቻላል ሲሉ ተናግሯል።

ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፀጥታ አካላት ላቅ ያለ ምስጋና በማቅረብ ሁላችንም በተባባረ ክንድ ይህንን ጊዜ መሻገር ይቻላል ብለዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ የትምሀርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶር ሙሉ ነጋ መንግስት ለትምህርት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶት በመስራት ላይ ይገኛል ሲሉ ተናግሯል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም በሰላምና ልማት ጉዳዩች ላይ መስራት እእዳለባቸውና ተማሪዎችም የሀገራቸውን ሰላም ሊጠብቁ ይገባል ብለዋል።

በብርሃኑ በጋሻውና ጀማል ከዲሮ

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.