Fana: At a Speed of Life!

የቻይና የመከላከያ ሚኒስቴር 200 ሺህ ዶዝ የኮቪድ 19 ክትባትለኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና የመከላከያ ሚኒስቴር 200 ሺህ ዶዝ ሲኖቫክስ የኮቪድ 19 ክትባት መድሀኒት ለኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና ወታደራዊ አታሼ ሲነር ኮሎኔል ሆንግ ዣንግ ቻይና ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል ፡፡

የጦር ሀይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ዶክተር ሀይሉ እንደሻው ቻይና ላደረገችው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ፡፡

አሁን የተገኘው ድጋፍም ለ100 ሺህ ሰዎች ሙሉ ክትባት መስጠት እንደሚያስችል የመከላከያ ጤና ማበልጸግ እና የበሽታ መከላከል መምሪያ ሀላፊ ተወካይ ኮሎኔል ዶክተር አለሙ ትኬ ተናግረዋል።

በግንባር ላይ ተሰማርቶ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ክትባቱን ለማጓጓዝና ለማዳረስ ከኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑንም መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.