Fana: At a Speed of Life!

መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና የወሰዱ የመንግስት ሠራተኞችና አመራሮች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና የወሰዱ 170 የክልሉ ጤና ቢሮና የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አመራሮችና ሰራተኞች ተመረቁ።

የምርቃት ስነ ስርዓቱ ዛሬ በባህርዳር ከተማ የተካሄደ ሲሆን÷ የተቋማቱ ሰራተኞችና አመራሮች መሰረታዊ የውትድርና ስልጠናውን በተግባርና በንድፈ ሀሳብ ለዘጠኝ ቀናት መውሰዳቸው ተገልጿል።

በጦርነቱ ሙያዊ ድጋፍ እያደረጉ የሚገኙት የሁለቱ ተቋማት ሰራተኞች በግንባር ለመሳተፍ የሚያስችል ስልጠና ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መልካሙ አብጤ በበኩላቸው÷ ሁልጊዜም ለድንገተኛ ሕክምና ከፊት የምትገኙ የጤና ባለሙያዎች ዛሬ ደግሞ የሌላ ሁለተኛ ሙያ ባለሙያ ባለቤት ሆናችኋል ብለዋል።

የሁለቱ ተቀማት አመራሮች እና ሰራተኞች በዚህ መልክ ለሀገራዊ ግዳጅ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው መመረቃቸው ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ የሚሆን ነውም ብለዋል።

በሀገር ላይ የተቃጣውን አደጋ ተከትሎ የሕክምና አገልግሎት ለሚሹ ወገኖች የጤና ባለሙያዎች ሙያዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዲቀጥሉ ሀላፊው ጥሪ አቅርበዋል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.