Fana: At a Speed of Life!

በነፋስ መውጫ የኤፍ-ኤች ኢትዮጵያ በአሸባሪው ቡድን ተዘረፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ ነፋስ መውጫ ከተማ የሚገኘው ኤፍ-ኤች ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ንብረቶች ውድመት እና ዘረፋ እንደተፈጸመባቸው የድርጅቱ ሃላፊ ተናግረዋል።
የኤፍ-ኤች ኢትዮጵያ የላይ ጋይንት ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አንተነህ አዳሙ እንዳሉት፥ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የሠራተኞች መኖሪያ ቤትን ጨምሮ፣ የእህል መጋዘኖች፣ በርካታ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።
የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች እና ጋራዥም ሙሉ በሙሉ ወድሟል ነው ያሉት።
መኪናን ጨምሮ 25 የፕሮጀክቱ የሞተር ሳይክሎች በወራሪው ቡድን መዘረፋቸውን ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
አቶ አንተነህ ለአደጋ ጊዜና ለሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚውል 4 ሺህ 551 ኩንታል በላይ እህል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን መወሰዱንም አረጋግጠዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.