Fana: At a Speed of Life!

የአሸባሪውን ህወሓት የጥፋት ተልዕኮ ለመመከት በየአካባቢው የተጠናከረ ጥበቃና ክትትል እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪውን ህወሓት የጥፋት ተልዕኮ ለመመከት በየአካባቢያቸው የተጠናከረ ጥበቃና ክትትል እያደረጉ መሆኑን የሠመራ-ሎጊያ ከተማ ወጣቶች ገለጹ፡፡

የሠመራ-ሎጊያ ከተማ ወጣቶች እንዳሉት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተለያዩ ጥፋቶችን እየፈጸመ ይገኛል፡፡

ቡድኑ በሰርጎ ገቦች ሠመራ-ሎጊያ ከተሞች ላይ እኩይ ተግባር እንዳይፈጽምና ህብረተሰቡ በተረጋጋ ሁኔታ የዕለት ተዕለት ኑሮውን እንዲመራ ሰላም በማስጠበቅ በተለይ ወጣቶች ተግባራቸውን እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

“በኢትዮጵያዊነታችን አንደራደርም” የሚሉት ወጣቶቹ÷ “የህዝቦችን አንድነትና አብሮ የመኖር እሴት ሊያሳጣ የተነሳውን አሸባሪ ለመከላከል ዝግጁ ነን” ብለዋል፡፡

አሸባሪው የሚነዛውን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በመተውና እርስ በእርስ በመተባበር ለአካባቢያቸው ሰላምና መረጋጋት የሚጠበቅባቸውን በማድረግ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ቡድኑን ለማጥፋት ተመሳሳይ አቋምና አስተሳሰብ እንዳላቸው ወጣቶቹ መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ለመከላከያ ሰራዊትና ለአፋር ልዩ ሃይል ወጣቶች ህብረተሰቡን በማስተባበር የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ መሆኑን ገልጸው÷ በተጨማሪ ለኢትዮጵያ ሲሉ መስዋዕትነት ለመክፍል ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡

የሰመራ-ሎጊያ ከተማ ከንቲባ አሊ መሃመድ÷ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ፀጥታ ለመጠበቅ በቁርጠኝነት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

እንደ ሠመራ ሎጊያ ከተማም ወጣቶች ካምፕ በመግባት አከባቢያቸውን ለመጠበቅ የሚያስችላቸው ስልጠና በመውሰድ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በሰመራ-ሎጊያ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊትና ለልዩ ሃይል 20 ሚሊየን ብር በገንዘብና 2ሚሊየን ብር የሚገመት ቁሳቁስ ተሰብስቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.