Fana: At a Speed of Life!

ለመከላከያ ሠራዊት ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ቃል ተገባ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ቃል መገባቱ ተገለፀ፡፡

በዞንም 351 በሬ ከየወረዳዎቹ ማሰባሰብ መቻሉ ተገልጿል፡፡

በዞኑ የሚገኙ 1 ሺህ 673 አመራሮች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመሰጠት ቃል የገቡ ሲሆን÷ 29 ሺህ 803 የመንግስት ሠራተኞችም ከደመወዛቸው 20 በመቶ ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡

በአጠቃላይ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አሰፈላጊ ነገሮችን ለመግዛት ከ48 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉንም የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የድጋፍ አሰባሰብ ምክትል ኃላፊ አቶ አበባየሁ ኤርምያስ ተናግረዋል፡፡

በማቱሣላ ማቴዎስ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.