Fana: At a Speed of Life!

ሽብርተኞቹን ህወሓትንና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ በጌዴኦ ዞን ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድን የሆኑትን ህወሓትንና ሸኔን የሚያወግዝና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ተካሄደ፡፡

ነዋሪዎቹ በሰልፉ ሀገሪቱን ከጥፋት ሀይሎች ለመታደግና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ እስከ ህይወት መስዋዕትነት ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል ።

የክደት ሃይሎቹ በኢትዮጵያ የወጠኑትን እኩይ ተግባር በተባበር ክንድ ይፈርሳል ሲሉ ባሳዩት መፈክር ገልጸዋል ።

ኢትዮጵያ ከፈተናዎቹ በላይ ሀያል ሀገር ናት ያሉት ነዋሪዎቹ በሽብር ቡዱኑ ምክንያት እንደማትፈርስ በመግለጽ ሀገር እያስከበረ ላለው ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለፃቸውን ከጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.