Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርጉ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተደረገውን ጥሪ ተከትሎ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡
በዚህም ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የንጽህና መጠበቂያ፣ የቤት ቁሳቁስ እና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጉን ከደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የተደረገውን የቁሳቁስ ድጋፍ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ፈንታ እና የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ አቶ ክንድዬ አይችሉህም ተረክበዋል።
ድጋፉ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲውል የተበረከተ ነው ያሉት አቶ ክንድዬ÷ ለተደረገው ድጋፍም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲን አመስግነዋል፡፡
ከዚህ በፊት ጂማ፣ መቱ፣ ጎንደር፣ ወልቂጤ፣ ቦንጋ፣ ወራቤ፣ ዋቻሞ እና ወለጋ ዩኒቨርሲቲዎች የተለያየ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.