Fana: At a Speed of Life!

በሀረር ለአገር መከላከያ ሰራዊት አጋርነትን ለመግለጽ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “የትም፣ መቼም፣ በምንም ለኢትዮዽያ እዘምታለው” በሚል መሪ ሀሳብ በሐረር ከተማ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ።
ለጀግናው የአገር መከላከያ አጋርነትን የመግለጽ ዓላማ ባለው በዚህ የሩጫ ውድድር ላይ የክልሉ ነዋሪዎች፣ አትሌቶችና በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላት ተሳትፈዋል።
መነሻውንና መድረሻውን የክልሉ ትምህትት ቢሮን ያደረገው የሩጫ ውድድር በህጻናት፣ በአዋቂዎችና በአትሌቶች ዘርፍ የተካሄደ ነው።
በአትሌቶች መካከል በተካሄደ ውድድር በወንዶች ሳዳም አብዱለጢፍ፣ ጃፈር በከርና ሙሉጌታ ፈጠነ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ሲያጠናቅቁ፤ በሴቶች አዚዛ ሙክታር፣ ሲሃም ሱፍያንና ያምላክስራ አበበ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ወጥተዋል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሐረሪ ጉባዔ ምክትል አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ደሊላ ዩስፍ እንደተናገሩት፤ የክልሉ ህዝብ ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት ደጀን በመሆን ስንቅ በማዘጋጀት፣ ደም በመለገስና የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
አሸባሪው ህወሃት እንኪደመሰስ ድረስ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል።
የሐረሪ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ያሲን ዩስፍ በበኩላቸው ነዋሪው ለአገር ሰላምና ሉዓላዊነት መከበር በጦር ግንባር ደሙን እያፈሰሰና ህይወቱን እየሰዋ ላለው የመከላከያ ሰራዊት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የዜግነት ግዴታውን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
የህዝቡ የደጀንነት ተግባር በቀጣይም በተለያዩ የድጋፍና የቅስቀሳ ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልማመላከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ የሜዳሊያ ሽልማት ከዕለቱ ክብር እንገዶች ተበርክቶላቸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.